በኃይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፥ ዐይኖቹ ወደ አሕዛብ ይመለከታሉ፥ ዓመፀኞች ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያድርጉ።
በኀይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፤ እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ። ሴላ
በኀይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፤ በዐይኑም መንግሥታትን አተኲሮ ያያል፤ ስለዚህ ዐመፀኞች በእርሱ ላይ ባይነሡ ይሻላቸዋል።
እግዚአብሔር ይባርከናል፥ የምድርም ዳርቻዎች ሁሉ ይፈሩታል።
ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”
ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ እርሱንስ ተዳፍሮ በደኅና የቆየ ማን ነው?
ጌታ በተቀደሰው መቅደሱ ነው፥ ጌታ፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፥ ዐይኖቹ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የመድኃኒቴ ጉልበት፥ በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንህ።
መንግሥትህ የዘለዓለም መንግሥት ናት፥ ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው።
ጌታ ከሰማይ ተመለከተ፥ የሰውንም ልጆች ሁሉ አየ።
ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፥ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኩራ።
ቀንዳችሁን እስከ ላይ አታንሡ፥ በእብሪተኛ አንገት አትናገሩ።
በትዕቢት ባደረጉባቸው ነገር ላይ ጌታ ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ አሁን አወቅሁ።”
ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።
ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’