መዝሙር 64:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በሮሮዬ ድምፄን ስማ፥ ከጠላትም ፍርሃት ነፍሴን አድን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከክፉዎች አድማ ሰውረኝ፤ ከዐመፀኞችም ሸንጎ ጋርደኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከክፉዎች ምሥጢራዊ ሤራና ከክፉ አድራጊዎች ዕቅድ ጠብቀኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አንተ የሚመጣ የሰውን ሁሉ ጸሎት ስማ |
ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፥ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፥ በበረሃም አገር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፤ እነርሱም፦ “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታወስ ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
አንተ ግን፥ አቤቱ! እኔን ለመግደል በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውን ይቅር አትበል፥ ኃጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህም ይውደቁ፥ በቁጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።