ርኅራኄህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላለችና፥ እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።
አምላክ ሆይ! ከሰማያት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም ከምድር ሁሉ በላይ ይሁን።
ሰውም፥ “በእውነት ለጻድቅ ፍሬ አለው፤ በእውነት በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላል።
በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም የሰወርሃት፥ ቸርነትህ እንደምን በዛች!
ነፍሴን ከአንበሶች መካከል አዳናት። ደንግጬ ተኛሁ፥ የሰው ልጆች ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ፥ አንደበታቸው የተሳለ ሾተል ነው።
እኔ ግን ለኃይልህ እቀኛለሁ፥ በምሕረትህም ማልዶ ደስ ይለኛል፥ በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና አምባዬ ሆነኸኛልና።
ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት፥ የዳዊት መዝሙር።
የሰማይንም ወፎች የባሕርንም ዓሦች፥ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።