አንደበትህ ጥፋትን ያስባል፥ እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግህ።
አንተ አታላይ አንደበት ሆይ፤ ጐጂ ቃላትን ሁሉ ወደድህ!
አንተ አታላይ ሰው ሰዎችን የሚጐዳ ቃል መናገር ትወዳለህ!
ሕዝቤን እንጀራን እንደ መብላት የሚበሉ ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁም እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
ስለ ሽንገላ አንደበት ምንን ይሰጡሃል? ምንስ ይጨምሩልሃል?
ምላሳቸውን እንደ እባብ ሳሉ፥ ከከንፈራቸው በታች የእፉኝት መርዝ አለ።
አፍህ ክፋትን አበዛ፥ አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ።