ሮቤልም መልሶ፥ “በዚህ ልጅ ላይ፥ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።
መዝሙር 51:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የድነቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤ አንደበቴም ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤቱ አዳኜ አምላኬ ሆይ! ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤ ስለ አዳኝነትህም የምስጋና መዝሙር እዘምራለሁ። |
ሮቤልም መልሶ፥ “በዚህ ልጅ ላይ፥ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።
ታዲያ በፊቱ ክፉ ነገር በማድረግ፥ የጌታን ቃል ያቃለልኸው ስለምንድን ነው? ሒታዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታህ፤ ሚስት እንድትሆንህም ሚስቱን ወሰድሃት፤ እርሱንም በአሞናውያን ሰይፍ ገደልኸው።
በዳዊት ዘመነ መንግሥት፥ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊት ጌታን ጠየቀ፤ ጌታም፥ “ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፥ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ።
በክፉ ሥራችንና በታላቁ በደላችን ከደረሰብን ነገር ሁሉ በኋላ፥ አንተ አምላካችን እንደ ኃጢአታችን ብዛት አልቀሠፍኸንም ነገር ግን ትሩፋንን ሰጠኸን።
ኃጢአተኛውን ሰው፦ ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ በምለው ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ ባታስጠነቅቀው ያ ኃጢአተኛ ሰው በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
ነገር ግን በተቃወሙትና በተሳደቡ ጊዜ፥ ልብሱን እያራገፈ “ደማችሁ በራሳችሁ ነው፤ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ፤” አላቸው።