22 አቤቱ፥ አንተ አትጣለኝ፥ አምላኬ፥ ከኔ አትራቅ።
22 ጌታዬ መድኅኔ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
22 አዳኜ አምላኬ ሆይ! ፈጥነህ እርዳኝ።
የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ በፍጥነት ድረስልኝ፥ ወደ አንተ ስጮኽም የልመናዬን ድምፅ ስማ።
ጭንቀት ቀርባለችና የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ።
ሳይቀባ፥ የዳዊት መዝሙር። ጌታ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፥ የሚያስፈራኝ ማን ነው? ጌታ የሕይወቴ ከለላዋ ነው፥ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?
ቍጥር የሌለው ክፋት ከቦኛልና፥ ኃጢአቶቼ ያዙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል ከራሴ ጠጉር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፥ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ ዘወትር፦ ጌታ ታላቅ ይሁን ይበሉ።
ነፍሴ በጸጥታ እግዚአብሔርን ትጠብቅ የለምን? መድኃኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን በጸጥታ ጠብቂ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
ለመዘምራን አለቃ፥ ለመታሰቢያ፥ የዳዊት መዝሙር።
የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ ደስ ይበላቸው፥ ማዳንህን የሚወድዱ ሁልጊዜ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ።
አምላክ ሆይ፥ ከእኔ አትራቅ፥ አምላኬ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።”