አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ።
በጽዮን አካባቢ ተመላለሱ፤ ዙሪያዋንም ሂዱ፤ የጥበቃ ግንቦቿንም ቍጠሩ፤
ተሰልፋችሁ ጽዮንን ዙሩአት፤ ማማዎችዋንም ቊጠሩ።
ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አላወቀም፤ ልብ እንደሌላቸው እንስሶችም ሆነ፥ መሰላቸውም።
አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፥