አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “ጌታ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ሶርያውያን ጌታ የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም’ ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ ጌታ መሆኔን ታውቃላችሁ” አለው።
መዝሙር 46:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ፥ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ የያዕቆብም አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። |
አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “ጌታ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ሶርያውያን ጌታ የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም’ ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ ጌታ መሆኔን ታውቃላችሁ” አለው።
እርሱም እንዲህ አለ፦ “አቤቱ፥ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ! በሰማይ ያለህ አምላክ አንተ አይደለህምን? የአሕዛብንስ መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህምን? ኃይልና ሥልጣን በእጅህ ነው፥ ሊቋቋምህም የሚችል የለም።
ወደ እርሱም ጸለየ፤ እርሱም ተለመነው፥ ጸሎቱንም ሰማው፥ ወደ መንግሥቱም ወደ ኢየሩሳሌም መለሰው፤ ምናሴም እርሱ ጌታ አምላክ እንደሆነ አወቀ።
አቤቱ! ኃይሌ፥ አምባዬ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ፥ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር የማይረባቸውንም ወርሰዋል፤