ነፍሴንም የሚሹአት በረቱብኝ፥ መከራዬንም የሚፈልጉ ከንቱን ተናገሩ፥ ሁልጊዜም በሽንገላ ይመክራሉ።
እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቈሮ፣ አፉንም መክፈት እንደማይችል ዲዳ ሆንሁ።
እኔ ግን ሊሰማ እንደማይችል ደንቆሮ፥ ለመናገር እንደማይችል ድዳ ሰው ነኝ።
ወደማልመለስበት ሳልሄድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ።
ኃጢአተኞች ወጥመድን ዘረጉብኝ፥ ከትእዛዝህ ግን አልሳትሁም።
በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፥ ክፉ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ ሁሉ በአፌ ላይ ልጓም አኖራለሁ አልሁ።
ከመተላለፌ ሁሉ አድነኝ፥ የሞኞች መሳለቂያ አታድርገኝ።
ተጨነቀ፥ ተሰቀየም፥ አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤