የትዕቢት እግር አይምጣብኝ፥ የዐመጸኞችም እጅ አያስተኝ።
ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁና እንደ ተጋደሙ፣ ቍልቍልም እንደ ተወረወሩና መነሣት እንደማይችሉ ተመልከት!
ክፉዎች እንዴት እንደ ወደቁ እይ። እነሆ ተጥለዋል፤ መነሣትም አይችሉም።
ኀጢአተኛ ጻድቁን ይመለካከተዋል፥ ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያፋጫል።
ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም።
የሚከብቡኝ ራሳቸውን አነሡ፥ የከንፈራቸው ክፋት ይክደናቸው።
ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም።
ሸክምህን በጌታ ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል፥ ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም።
አሕዛብ በሠሩት ጉድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።
አንተም እንዲህ በል፦ ‘እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች አትነሣምም።’ ” የኤርምያስ ቃላት እስከዚህ ድረስ ነው።
አቤቱ፥ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፥ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኃይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፥ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።