መዝሙር 34:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንደበትህን ከክፉ ነገር፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን ከመናገር ከልክል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ፤ ሰላምን ፈልጋት፤ ተከተላትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከክፉ ነገር ሽሹ፤ መልካም ነገርንም አድርጉ፤ ሰላምን ፈልጉአት፤ ተከተሉአትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለወዳጆቼና ለወንድሞቼ እንደማደርግ አደረግሁ፤ እንደሚያለቅስና እንደሚተክዝ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረግሁ። |
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ በአንድ ልብ ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
ሆኖም የእግዚአብሔር ጠንካራ መሠረት የቆመው፦ “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለውን ማኅተም ታትሞ ነው።
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።