የሚፈሩት ምንም አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ ጌታን ፍሩት።
አንበሶች ሊያጡ፣ ሊራቡም ይችላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም።
የአንበሳ ደቦሎች ያጣሉ፤ ይራባሉም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ምንም አይጐድልባቸውም፤ መልካም ነገርም አያጡም።
አጥንቶች ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ድሃውን ከሚቀማው እጅ ድሃውንና ችግረኛውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።”
የአንበሳ ግልገሎች ለመንጠቅ ይጮኻሉ፥ ከእግዚአብሔርም ምግባቸውን ይሻሉ።
ክብርና ሀብት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
የዳዊት መዝሙር። ጌታ እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
ነፍሳቸውን ከሞት ያድን ዘንድ፥ በራብም ጊዜ በሕይወት ይጠብቃቸው ዘንድ።
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።
ጌታ የጻድቁን ነፍስ አያስርብም፥ የክፉዎችን ምኞት ግን ይገለብጣል።
ጌታን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፥ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፥ ክፉ ነገርም አያገኘውም።
የትሕትናና ጌታን የመፍራት ውጤት ሀብት፥ ክብርና ሕይወት ናቸው።
አሕዛብም እነዚህን ሁሉ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃል።