ጌታ ለሕዝቡ ኃይላቸው ነው፥ ለቀባውም የመድኃኒቱ መታመኛ ነው።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው፤ ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይላቸው ነው፤ ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥም የመዳኛ ከለላው ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ምድረ በዳውን ያናውጣል፥ እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
ጌታንም፦ አንተ አምላኬ ነህ፥ የልመናዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድምጥ አልሁት።
የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በጌታና በመሢሑ ላይ ተማከሩ፦
በማዳንህ ደስ ይለናል፥ በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፥ ልመናህን ሁሉ ጌታ ይፈጽምልህ።
ጌታ የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ አወቅሁ፥ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል፥ በቀኙ ብርታት ማዳን አለና።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ጌታ ቀብቶኛልና፥ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያ ቀን ጀምሮ የጌታ መንፈስ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ፤ ሳሙኤልም ወደ ራማ ተመለሰ።