እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፥ የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።
እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤ እናንተ የዘላለም በሮች፤ የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።
ለየዋሃን ፍርድን ያስተምራቸዋል፤ ለየዋሃን መንገድን ያመለክታቸዋል።
ይህች የጌታ ደጅ ናት፥ ወደ እርሷ ጻድቃን ይገባሉ።