እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፥ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዢዎች ሆኑ፤ ገበሩለትም።
መዝሙር 18:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፥ የባዕድ ልጆች ያጐነብሱልኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባዕዳን ፈሩ፤ ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፍርሃት ይጨነቃሉ፤ በመንቀጥቀጥም ከምሽጋቸው ወጥተው ወደ እኔ ይመጣሉ። |
እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፥ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዢዎች ሆኑ፤ ገበሩለትም።
ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው የሶርያውያን ግዛት የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ። ሶርያውያን ተገዙለት፤ ገበሩለትም። ጌታም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።
እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፥ በምድር እንደሚሳቡ ፍጥረታት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጋቸው ይመጣሉ፤ በፍርሃት ወደ ጌታ አምላካችን ይመጣሉ፥ ከአንተ የተነሣ ይፈራሉ።
እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፥ በጌታ የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፥ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።”