La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 147:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ የተዋረዱትን ያነሣል፥ ክፉዎችን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ትሑታንን ከፍ ያደርጋል፤ ክፉዎችን ግን ወደ ምድር ይጥላል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ትሑታንን ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ክፉ አድራጊዎችን ግን በምድር ላይ ጥሎ ያዋርዳቸዋል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በረ​ዶ​ውን እንደ ፍር​ፋሪ ያወ​ር​ዳል፤ ቅዝ​ቃ​ዜ​ው​ንስ ማን ይቋ​ቋ​ማል?

Ver Capítulo



መዝሙር 147:6
16 Referencias Cruzadas  

ጌታ በቃሎቹ የታመነ ነው፥ በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፥ ጌታ የሚወድቁትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥ ያጎነበሱትንም ያነሣቸዋል።


ጌታ በሕዝቡ ተደስቶአልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ያስጌጣቸዋል።


ትሑታንን በፍርድ ይመራል፥ ለትሑታን መንገድን ያስተምራቸዋል።


ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፥ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።


እኔንም ስለ ቅንነቴ ደገፍከኝ፥ በፊትህም ለዘለዓለም አጸናኸኝ።


ሸክምህን በጌታ ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል፥ ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም።


እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ፥ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ ጌታን ፈልጉ፤ ጽድቅን ፈልጉ፥ ትሕትናን ፈልጉ፤ ምናልባት በጌታ ቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።


እኔ በምሠራበት ቀን ክፉዎችን ትረግጧቸዋላችሁ፥ ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።


በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፥ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል።


ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጽሞና መንፈስ የተዋበው የተሰወረ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።


እንግዲህ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ ሥር ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ።


ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ሊያደርጋቸው፥ የክብርንም ዙፋን ሊያወርሳቸው፥ እርሱ ድኾችን ከትቢያ፥ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ የምድር መሠረቶች የጌታ ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አኖረ።