ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፥ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።
ቃሉን ልኮ ያቀልጣቸዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፤ ውሆችንም ያፈስሳል።
ከዚህ በኋላ ትእዛዝ ይሰጣል፤ የተጋገረውም በረዶ ይቀልጣል፤ ነፋስን ያነፍሳል፤ ውሃም ይፈስሳል።
ከእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ተሰጥቶአል፥ የውኆችም ስፋት ይጠጥራል።
በደቡብ ነፋስ ምድር ጸጥ ባለች ጊዜ፥ ልብስህ የሞቀች አንተ ሆይ፥
ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከአዘቅትም አዳናቸው።
መልእክቱን ወደ ምድር ይልካል፥ ቃሉም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል።
እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፥ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።
ከሰማይ የምሥራቅን ነፋስ አስነሣ፥ በኃይሉም የደቡብን ነፋስ አመጣ፥