ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም እንደሚፈስስ፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።
በራስ ላይ ፈስሶ፣ እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣ እስከ አሮን ጢም እንደሚወርድ፣ እስከ ልብሱም ዐንገትጌ እንደሚደርስ ውድ ሽቱ ነው።
በአሮን ራስና ጢም ላይ እንደሚፈስስ፥ እስከ ልብሱም ዘርፍ ድረስ እንደሚዘልቅ፥ መልካም መዓዛ እንዳለው የወይራ ዘይት ነው።
በሌሊት በቤተ መቅደስ እጆቻችሁን አንሡ፥ እግዚአብሔርንም አመስግኑት።
ጻድቅ በጽኑ ፍቅር ይገሥጸኝ፥ ይዝለፈኝም፥ የክፉ ሰው ዘይት ግን ራሴን አይቀባ፥ ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነውና።
በታችኛው ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃ ሮማኖች አድርግ፤ በዚያም መካከል በዙሪያው የወርቅ ሻኩራዎች አድርግ፤
የቅባትን ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈስሰዋለህ፥ ትቀባዋለህም።
ቀማሚ እንደሚቀምመው፥ በጨው የተቀመመ፥ ንጹሕና ቅዱስ አድርገህ ዕጣን አዘጋጅ።
በቀሚሱ ታችኛው ዘርፍ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ በፍታ ሮማኖችን አደረጉ።
ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፥ ነፍስም በወዳጅ ምክር ደስ ይላታል።
ዘይትህ መልካም መዓዛ አለው፥ ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፥ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።
ከቅባቱም ዘይት በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰ፥ እንዲቀደስም ቀባው።
ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቶ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጉርዋም አበሰቻችው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።