በመንገድም የሚያልፉ፦ የጌታ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፥ በጌታ ስም እንመርቃችኋለን አይሉም።
መንገድ ዐላፊዎችም፣ “የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን” አይበሉ።
በአጠገባቸው የሚያልፉት ሁሉ ለጽዮን ጠላቶች “እግዚአብሔር ይባርካችሁ! እኛም በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን!” አይሉአቸውም።
እርሱም እስራኤልን ከኀጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።
ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ሕዝቡን በሠራዊት ጌታ ስም ባረከ።
በጌታ ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፥ ከጌታ ቤት መረቅናችሁ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላም፥ ቦዔዝ ከቤተልሔም መጣ፥ አጫጆችንም፦ “ጌታ ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው። እነርሱም፦ “ጌታ ይባርክህ” ብለው መለሱለት።