መሄድስ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፥ መመለስስ፥ ነዶአቸውን ተሸክመው በእልልታ ይመጣሉ።
ዘር ቋጥረው፣ እያለቀሱ የተሰማሩ፣ ነዷቸውን ተሸክመው፣ እልል እያሉ ይመለሳሉ።
ዘሩን ተሸክመው ሲሄዱ ያለቅሱ የነበሩት፥ በደስታ እየዘመሩ ነዶአቸውን ተሸክመው ይመለሳሉ።
ቅዱሳን ሆይ፥ ለጌታ ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።
ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፥ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን፥ ልቅሶ ማታ ይመጣል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።
ጌታ ለክብሩ የተከላቸው ጽድቃዊ የባሉጥ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች በአመድ ፋንታ አክሊልን እንዳደርግላቸው፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘን መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እንድሰጣቸው ልኮኛል።