ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዐይኖቼን መልስ፥ በመንገድህ ሕያው አድርገኝ።
ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ፤ በራስህ መንገድ እንደ ገና ሕያው አድርገኝ።
ወደ ከንቱ ነገር ከማዘንበል ጠብቀኝ፤ በቃልህ መሠረት ሕይወቴን አድስልኝ።
አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።
“ከዐይኖቼ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፥ እንግዲህ ቈንጆይቱን እንዴት በፍትወት እመለከታለሁ?
ነፍሴ ወደ አፈር ተጠጋች፥ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
እነሆ፥ ትእዛዝህን ናፈቅሁ፥ በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ።
ብዙ ጭንቀትንና መከራን አሳይተኸኛልና፥ ተመለስህ ሕያውም አደረግኸኝ፥ ከምድር ጥልቅም እንደገና አወጣኸኝ።
ቀና ብለህ እያየኸው ይጠፋል፥ ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና።
ዐይኖችህ አቅንተው ይዩ፥ አተኩረው ፊት ለፊት ይመልከቱ።
በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በጭቆና የሚገኝ ትርፍን የሚጸየፍ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚሰበስብ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚከልል፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።
ዘርፉንም በልብሳችሁ ላይ አኑሩት እርሱንም በተመለከታችሁ ጊዜ የጌታን ትእዛዝ ሁሉ ታስታውሳላችሁ ታደርጉታላችሁም፥ ምኞታችሁንም በመከተል ያመነዘራችሁባትን የልባችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ የማትከተሉ ትሆናላችሁ።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወደ ሴት አይቶ የተመኛት ሁሉ ከወዲሁ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሮአል።
በምርኮ መካከል አንድ ያማረ የሰናዖር ካባ፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም ኀምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም፤ እነሆም፥ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ በታች ነው።”
ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፥ የሥጋ ምኞት፥ የዐይን ምኞት፥ በኑሮ ደረጃ መመካት፥ ከዓለም ነው እንጂ ከአብ አይደለም።