38 እንዲፈራህ ባርያህን በቃልህ አጽና።
38 ትፈራ ዘንድ፣ ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል ፈጽም።
38 ለእኔ ለአገልጋይህና ለሚፈሩህ ሁሉ የሰጠኸውን የተስፋ ቃል ፈጽም።
ጌታ በሚፈሩት፥ በጽኑ ፍቅሩ በሚታመኑት ይደሰታል።
እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ “አዎን” ማለት የእርሱ ነው፤ ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር ክብር በእኛ ስለሚነገረው “አሜን” የምንለው እርሱ በኩል ነው።
የጌታ ጽኑ ፍቅር ግን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚፈሩት ላይ፥ ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፥
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ጌታም ለሚፈሩት ይራራል፥
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ።
ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያሳካል፥ ጩኸታቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም።
ለባርያህ የሰጠኸውን የተስፋ ቃልህን አስብ።
አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ! አገልጋይህ ለነበረው ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ሁሉ እንዲፈጸም አድርግ።
ቃልህ ሕያው አድርጎኛልና ይህች በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።
ምሕረትህ ለመጽናናቴ ትሁነኝ፥ እንደ ቃልህም ለባርያህ ይሁነው።
ፍርዴን ፍረድ አድነኝም፥ ስለ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።