አንቺ ባሕር የሸሸሽው፥ አንቺስ ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽው፥ ምን ሆናችሁ ነው?
አንቺ ባሕር፤ የሸሸሽው አንቺም ዮርዳኖስ ያፈገፈግሽው ለምንድን ነው?
አንተ ባሕር፥ ምን ሆነህ ሸሸህ? አንተስ ዮርዳኖስ፥ ስለምን መፍሰስህን አቁመህ ወደ ኋላህ ተመለስህ?
እግዚአብሔር መሓሪና ጻድቅ ነው። አምላካችን ይቅር ባይ ነው።
ጌታ ሆይ ንዴትህ በወንዞች ላይ ነውን? ወይስ ቁጣህ በወንዞች ላይ ወይም መዓትህ በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህ፥ በማዳን ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና።