መዝሙር 113:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት። ሃሌ ሉያ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤ ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል። ሃሌ ሉያ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መኻኒቱንም በቤቷ በክብር ያኖራታል፤ ልጆችንም በመስጠት ደስ ያሰኛታል። እግዚአብሔር ይመስገን! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ፥ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህም ምስጋናን እንስጥ |
አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል ጌታ።
“አንቺ የማትወልጅ መካን! ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ! እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና” ተብሎ ተጽፎአልና።
ጠግበው የነበሩ አጥተው ለእንጀራ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን ከራብ ዐርፈዋል። መካኒቱ ሰባት ወለደች፥ ብዙ የወለደችው ግን ብቻዋን ቀረች።