La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 109:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልጆቹም እጅጉን ይቅበዝበዙ፥ ይለምኑም፥ ከፈራረሱ ቤቶቻቸውም ሳይቀር ይባረሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ልጆቹ ይንከራተቱ፤ ለማኞችም ይሁኑ፤ ከፈረሰው ቤታቸውም ይሰደዱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ልጆቹ ቤት የሌላቸው ለማኞች ይሁኑ፤ አሁን ከሚኖሩበት ፍርስራሽ ቤት እንኳ ይባረሩ።

Ver Capítulo



መዝሙር 109:10
10 Referencias Cruzadas  

ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ከኢዮአብ ቤት ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት፥ በምርኲዝ የሚሄድ አንካሳ፥ ወይም በሰይፍ ተመቶ የሚሞት ወይም የሚበላው ያጣ ራብተኛ አይታጣ።”


ከዚህም የተነሣ እነሆ፥ የንዕማን የቆዳ በሽታ ወደ አንተ ይተላለፋል፤ አንተና ዘሮችህ ለዘለዓለም ከዚያ በሽታ አትነጹም!” አለው። ግያዝም ወጥቶ ሲሄድ፥ ያ የቆዳ በሽታ ስለ ተጋባበት ገላው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።


ልጆቹ ቢበዙ በሰይፍ ይሞታሉ፥ ዘሩም በቂ እንጀራ ከቶ አያገኝም።


ልጆቹም ከደኅንነት ርቀዋል፥ በበርም ውስጥ ተረግጠዋል፥ የሚደርስላቸውም የለም።


ጐለመስሁ አረጀሁም፥ ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።


ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ።


ከጎጆቸው ተበትነው እንደሚበሩ ወፎች፥ የሞዓብ ሴቶችም በአርኖን መሻገሪያዎች እንዲሁ ይሆናሉ።