በምድረ በዳም በምኞትን ተቃጠሉ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
በምድረ በዳ እጅግ መመኘት አበዙ፤ በበረሓም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
በበረሓ ሳሉ ብዙ ነገር ተመኙ፤ እግዚአብሔርንም ተፈታተኑት።
ከጨለማና ከሞት ጥላ አወጣቸው፥ እግር ብረታቸውንም ሰበረ።
ከወደዱትም አላሳጣቸውም፥ መብላቸውም ገና በአፋቸው ሳለ፥
ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፦ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉት። ሙሴም፦ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? ጌታንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
በእነርሱም መካከል የነበረው የተለያየ ሕዝብ እጅግ ጐመጀ፤ የእስራኤልም ልጆች ዳግመኛ ዘወር በለው አለቀሱ እንዲህም አሉ፦ “የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል?
በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ክብሬንና ተአምራቴን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ እኔን ስለ ተፈታተኑኝ፥ ድምፄንም ስላልሰሙ፥
እነርሱ ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛም እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ምሳሌ ሆኑልን።
ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑትና በእባቦች እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን።
“እንደገና በታቤራ፥ በማሳህም፥ በቂብሮት ሐታዋም ጌታን አስቆጣችሁት።