መዝሙር 105:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሕዛብንም አገሮች ሰጣቸው፥ ከሕዝቦችም ድካም ወረሱ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሌሎችን ሕዝቦች ምድር ሰጣቸው፤ የእነዚህንም የድካም ፍሬ ወረሱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሌሎች ሕዝቦችን ምድር ሰጣቸው፤ ሌሎች የደከሙባቸውንም እርሻዎች አወረሳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ተጨነቁም ተመለከታቸው፥ ጸሎታቸውንም ሰማቸው፤ |
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ድምፅህን አልሰሙም በሕግህም አልሄዱም፥ እንዲያደርጉም ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።
ጌታም ለሙሴ እንደ ተናገረው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደየነገዳቸው ድርሻ ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
እነሆ፥ እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ በፀሐይ መግቢያ እስካለው እስከ ታልቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ የቀሩትን እነዚህን አሕዛብ በዕጣ ሰጠኋችሁ።
እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተዋጉ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ፥ ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።