የአገራቸውንም ተክሎች ሁሉ በላ፥ የምድራቸውንም ፍሬ በላ።
የምድሪቱንም ዕፀዋት ሁሉ በላ፤ የመሬታቸውንም ፍሬ ሙጥጥ አደረገ፤
በምድሩ ላይ ያለውን ለምለም ተክልና ሰብል ሁሉ በልተው እንዲጨርሱ አደረገ፤
ከአሕዛብ ጋር ተደባለቁ፥ ሥራቸውንም ተማሩ።
የምድሩንም ፊት ሸፈኑት ምድሪቱም ጨለመች፤ የአገሪቱን ቡቃያ ሁሉ በረዶውም የተወውን በዛፉ የነበረውን ፍሬ ሁሉ በሉ፤ ለምለም ነገር በዛፉ ላይም በቡቃያው ላይም በግብጽ ምድር ሁሉ አልቀረም።