ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፥ የአገራቸውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።
ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፤ የአገራቸውንም ዛፍ ከተከተ።
የወይን ተክሎቻቸውንና የበለስ ዛፎቻቸውን አጠፋ፤ ሌሎቹንም ዛፎቻቸውን ሁሉ ሰባበረ።
መንፈሱን አስመርረዋታልና፤ በከንፈሮቹም አዘዘ።
ወይናቸውን በበረዶ፥ በለሳቸውንም በአመዳይ አጠፋ።
የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተነገራቸው።