La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 10:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፍርዱ ለወላጅ አልባና ለተጨቆነ ይደረግ ዘንድ፥ ሰዎች በምድር ላይ ማሸበራቸውን እንዳይቀጥሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዐፈር የተፈጠረ ሰው ከእንግዲህ እንዳያስጨንቃቸው፣ አንተ ለድኻ አደጉና ለተገፋው ትሟገታለህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ሌሎችን ለማስፈራራት እንዳይችል፥ አንተ ለወላጅ አልባና ለተጨቈኑ ሰዎች ትከላከላለህ።

Ver Capítulo



መዝሙር 10:18
13 Referencias Cruzadas  

አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቁጣን ትመለከታለህና በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት፥ ምስኪን እራሱን ለአንተ አሳልፎ ይሰጣል፥ ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።


አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።


ለችግረኞች ሕዝብ በጽድቅ ይፍረድ፥ የድሆችንም ልጆች ያድን፥ ጨቋኙንም ይጨፍልቅ።


ችግረኛ አፍሮ አይመለስ፥ ችግረኛና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።


ለድሆችና ወላጅ ለሞተባቸው ፍረዱ፥ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ፍትሕን አድርጉ፥


እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥ አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል።


ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።


አብርሃም ግን ‘ልጄ ሆይ! አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም ነገሮችህን እንደተቀበልህ አስብ፤ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል፤ አንተም ትሠቃያለህ።


ወላጁን ላጣና ለመበለቲቱ ይፈርዳል፥ ስደተኛውንም ስለሚወድ ምግብና ልብስ ይሰጠዋል።