ምሳሌ 8:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና። ከጌታም ሞገስን ያገኛልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያገኘኝ ሁሉ ሕይወትን ያገኛልና፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ይቀበላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን የሚያገኝ፥ ሕይወትን ያገኛል፤ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ያገኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዶቼ የሕይወት መንገዶች ናቸውና። እኔን ያገኘ ሕይወትን አገኘ፤ ፈቃዱም በእግዚአብሔር ዘንድ ይዘጋጃል። |
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ ለማወቅ ስል ሁሉ ነገር ጉዳት እንደሆነ አድርጌ እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ነገሮች በማጣት ተጐዳሁ፤ እነርሱንም እንደ ጉድፍ አድርጌ ቈጠርኋቸው፤ በዚህም ክርስቶስን እንዳገኝ፥