ተግሣጼን እንጂ ብርን አትቀበሉ፥ ከተመረጠ ወርቅም ይልቅ እውቀትን ተቀበሉ።
ከብር ይልቅ ምክሬን፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ፤
ከብር ይልቅ ምክሬን ምረጡ፤ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ።
ከብር ይልቅ ትምህርትን፥ ከተፈተነ ወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ተቀበሉ።
በንጹሕ ወርቅ አትገኝም፥ ዋጋዋም በብር አይተመንም።
ወርቅና ብርጭቆ አይወዳደሩአትም፥ ከጥሩ ወርቅ በተሠራ ዕቃም አትለወጥም።
ስለዚህ ከወርቅና ከዕንቁ ይልቅ ትእዛዝህን ወደድሁ።
ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።
ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል። ዮድ።
የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው፥ የክፉ ልብ ግን ዋጋ ቢስ ነው።
ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።
ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቁ ይገኛል፥ የእውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።
እውነትን ገንዘብህ አድርግ፥ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም ግዛ።
ፍሬዬም ከምዝምዝ ወርቅ ይሻላል፥ ቡቃያዬም ከተመረጠች ብር።
ጥበብ ከርስት ጋር መልካም ነው፥ ፀሐይንም ለሚያዩ ሰዎች ትርፍን ይሰጣል።
ጴጥሮስ ግን “ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ፤” አለው።
ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድኾች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።