ምሳሌ 7:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁከተኛና እንቢተኛ ናት፥ እግሮችዋም በቤትዋ አይቀመጡም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ናት፤ እግሮቿ ዐርፈው ቤት አይቀመጡም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋ ደፋርና ኀፍረተቢስ ሴት ነበረች፤ በቤትዋ መቀመጥ ስለማያስደስታት ዘወትር ትዞራለች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁከተኛና አበያ ናት፥ እግሮችዋም በቤቷ አያርፉም፥ |
እንዲሁም በእነርሱ አማካይነት የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚቈጣጠሩ፥ ንጹሖች፥ በቤታቸው ውስጥ ሥራቸውን በደንብ የሚያከናውኑ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው።