ምሳሌ 6:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብሏን በበጋ ታሰናዳለች፥ መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም ግን በበጋ ምግቡን ያከማቻል፤ በመከርም ወቅት ቀለቡን ይሰበስባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በበጋ ወራት ምግባቸውን ያከማቻሉ፤ በመከር ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ይሰበስባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መብሉን በበጋ ይሰበስባል፥ በመከርም ጊዜ በሰፊ ቦታ ያስቀምጣል። ወይም ወደ ንብ ሂድ፥ ሠራተኛ እንደ ሆነች፥ መልካም ሥራንም እንደምትሠራ ዕወቅ፥ የደከመችበትንም ነገሥታትና ሌሎች ሰዎች ለጤንነት ይወስዱታል። በሁሉም ዘንድ የተወደደች ናት፥ የከበረችም ናት። በአካሏ ደካማ ናት፥ በሥራዋ ግን የጸናች ናት፥ ጥበብን አክብራ አሳየች። |