ምሳሌ 6:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁስልንና ውርደትን ያገኛል፥ ስድቡም አይደመሰስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መደብደብና ውርደት ዕጣው ነው፤ ኀፍረቱም ከቶ አይወገድም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውርደትና ድብደባ ይደርስበታል፤ ሁልጊዜም እንደ ተዋረደ ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍስልንና ውርደትን ያገኛል፥ ስድቡም ለዘለዓለም አይደመሰስም። |
ጌታ ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሒታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር ጌታን ደስ የሚያሰኝ ነገር በማድረጉና ትእዛዙንም በብርቱ ጥንቃቄ በመጠበቁ ነው።
የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በዚህ ነገር ኃጢአት አድርጎ የለምን? በብዙ አሕዛብም መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፥ በአምላኩም ዘንድ የተወደደ ነበረ፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ሁሉ ላይ አንግሦት ነበር፥ እርሱንም እንኳ እንግዶች ሴቶች አሳቱት።