የቤት አገልጋዮቿን ጠራች፤ እንዲህም አለቻቸው፤ “አያችሁ፤ ለካስ ይህ ዕብራዊ የመጣው መሣለቂያ ሊያደርገን ኖሮአል! እዚህ ድረስ ሰተት ብሎ ገብቶ ካልተኛሁሽ አለኝ፤ እኔም ጩኸቴን ለቀቅሁት፤
ምሳሌ 6:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሴተኛ ዐዳሪዋ ዋጋ እስከ አንዲት እንጀራ ነው፥ አመንዝራም ሴት የሰውን ሕይወት ታጠምዳለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጋለሞታ ሴት ቍራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤ አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ወንድ ሴትኛ ዐዳሪዋን በአንድ እንጀራ ዋጋ ሊያገኛት ይችላል፤ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ማመንዘር ግን የሕይወት ዋጋ ያስከፍላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአመንዝራ ሴት ክብር እስከ አንዲት እንጀራ ነው፤ አመንዝራ ሴትም የተከበሩ ወንዶች ነፍስን ታጠምዳለች። |
የቤት አገልጋዮቿን ጠራች፤ እንዲህም አለቻቸው፤ “አያችሁ፤ ለካስ ይህ ዕብራዊ የመጣው መሣለቂያ ሊያደርገን ኖሮአል! እዚህ ድረስ ሰተት ብሎ ገብቶ ካልተኛሁሽ አለኝ፤ እኔም ጩኸቴን ለቀቅሁት፤
እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስን ለማጥመድ ለእጅ ድጋፍ መከዳ ለሚሰፉ ለሰውም ሁሉ ራስ እንደየቁመቱ ሽፋን ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤንም ነፍስ ብታጠምዱ በውኑ ነፍሳችሁን ታድናላችሁን?
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከንቱ ነገርን ስለ ተናገራችሁ፥ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ፥ እነሆ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፤ በፊቱም ሰግዶ፦ ቁራሽ እንጀራ እንድበላ ከካህናት ስፍራ ወደ አንዲቱ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ የዕለት ምግብ ብቻ ለማግኘት ይለምናል።’”