ጠማማነት በልቡ አለ፥ ሁልጊዜም ክፋትን ያቅዳል፥ ጠብንም ይዘራል።
በልቡ ተንኰል ክፋትን የሚያውጠነጥን፣ ምን ጊዜም ጠብ ይጭራል።
በጠማማ አእምሮው ዘወትር ክፉ ነገርን ለማድረግ ያቅዳል፤ ሁልጊዜ ጠብን ይዘራል።
ጠማማ ልቡ ሁልጊዜ ክፋትን ያስባል፤ እንደዚህም ያለ ሰው ጠብን በከተማ ላይ ይዘራል።
አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድነኝ፥ ከዓመፀኞች ሰዎች ጠብቀኝ
በልባቸውም ክፉ ካሰቡ፥ ቀኑን ሁሉ ለሰልፍ ከሚከማቹ።
የአፉ ቃል ግፍና ሽንገላ ነው፥ ማስተዋልን በጎ ማድረግንም ተወ።
ክፉ የሚያደርጉ ይስታሉ፥ ምሕረትና እውነት ግን መልካምን ለሚያደርጉ ናቸው።
ምናምንቴ ሰው ክፋትን ይምሳል፥ በከንፈሩም የሚቃጠል እሳት አለ።
ጠማማ ልብ ያለው መልካምን አያገኝም፥ ምላሱንም የሚገለብጥ በክፉ ላይ ይወድቃል።
ክፉ በመሥራት ደስ የሚላቸው በጠማማነትም ሐሤትን የሚያደርጉ፥
የበደለኛ መንገድ የጠመመች ናት፥ የንጹሕ ሥራ ግን የቀና ነው።
ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የቁጣውም በትር ይጠፋል።
ክፉ ለማድረግ የሚያውጠነጥን፥ ተንኰለኛ ይባላል።
እርሱ ተማምኖ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ፥ በወዳጅህ ላይ ክፉ አትሥራ።
ጠማማ ሁሉ በጌታ ፊት ርኩስ ነውና፥ ወዳጅነቱ ግን ከቅኖች ጋር ነው።
የሸንጋይ ሽንገላ ክፉ ናት፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆንም እንኳን በሐሰት ቃል ድሀውን ለማጥፋት ክፉን አሳብ ያስባል።
ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ሊል አይችልምና፥ ውኆቹም ጭቃና ጉድፍ ያወጣሉ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ክፋትን የሚያቅዱና በዚህችም ከተማ ክፉ ምክርን የሚመክሩ ሰዎች ናቸው።
ነፋስን ዘሩ፥ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ የቆመውም እህል ዛላ የለውም፥ ከእርሱም ዱቄት አይገኝም፤ ቢገኝም እንኳ ባዕዳን ይበሉታል።
ክፋትን ለማድረግ በምስጢር ለሚያቅዱና በመኝታቸው ላይ ክፋ ነገርን ለሚሠሩ ወዮላቸው! ሲነጋ ይፈጽሙታል፥ ኃይል በእጃቸው ነውና።
ወንድሞች ሆይ! ከሚለያዩትና እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም መሰናክል ከሚያደርጉ ሰዎች እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ፤