La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የቀና የሕይወትን መንገድ አታገኝም፥ በአካሄድዋ የተቅበዘበዘች ናት፥ የሚታወቅም አይደለም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለ ሕይወት መንገድ ደንታ የላትም፤ መንገዶቿ ዘወርዋራ ናቸው፤ ለርሷ ግን አይታወቃትም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደ ሕይወት በሚመራው መንገድ አትሄድም፤ እንዲሁ ትባዝናለች፤ መባዘንዋን ግን አታውቀውም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሕይወት መንገድም አትሄድም። መሮጫዋ ሰንከልካላ ነው፥ የሚታወቅም አይደለም።

Ver Capítulo



ምሳሌ 5:6
12 Referencias Cruzadas  

ስለ መንገዶችህ አሰብሁ፥ እግሬንም ወደ ምስክሮችህ መለስሁ።


የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፥ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘለዓለም ፍሥሐ አለ።


በጽድቅ የሚጸና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፥ ክፋትን የሚከተል ግን ወደ ሞት ይሄዳል።


ወደ እርሷ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥ ወደ ሕይወት ጎዳናም አይደርሱም፥


የአመንዝራ ሴት መንገድም እንዲሁ ነው። በልታ አፍዋን የምታብስ፦ “አንዳች ክፉ ነገርም አላደረግሁም” የምትል።


የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና።


የሰው መንገድ በጌታ ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና።


አላዋቂ ሴት ሁከተኛ ናት፥ አሳብ የላትም፥ አንዳችም አታውቅም።


ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትንም የማይተዉ ዐይኖች አላቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።