ምሳሌ 31:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበፍታ ልብስ እየሠራች ትሸጣለች፥ ለነጋዴም ድግ ትሸጣለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበፍታ ልብስ እየሠራች ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታስረክባለች። |
ከምርትሽ ብዛት የተነሣ አራም ነጋዴሽ ነበረች፤ ዕቃዎችሽን በበሉር፥ በወይን ጠጅ፥ በወርቀ ዘቦ፥ በጥሩ በፍታም በዛጐልም በቀይ ዕንቁም ይቀይሩ ነበር።
ሳምሶን እንዲህ አላቸው፤ “እንድ እንቈቅልሽ እነግራችኋለሁ፤ ታዲያ ፍቺውን በሰርጉ በዓል ሰባት ቀኖች ውስጥ ከሰጣችሁኝ፥ ሠላሳ የቀጭን ፈትል በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ እሰጣችኋለሁ።