እርሱ ተማምኖ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ፥ በወዳጅህ ላይ ክፉ አትሥራ።
አንተን ተማምኖ በአጠገብህ በተቀመጠ፣ በጎረቤትህ ላይ ክፉ አትምከርበት።
አንተን ተማምኖ በአጠገብህ በሚኖረው ጐረቤትህ ላይ በተንኰል ክፉ ነገር ለማድረግ አታስብ።
እርሱ ተማምኖብህ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ፥ እንደገና በወዳጅህ ላይ ክፉ አታስብ፤
በእርጋታ በምድሪቱ ለተቀመጡት ሰላምን አይናገሩምና፥ በቁጣም ሽንገላን ይመክራሉ።
አይለወጡምና፥ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና ከጥንት ጀምሮ የነበረ እግዚአብሔር ሰምቶ ያጐሰቁላቸዋል።
ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥ ከደም ሰዎችም አድነኝ።
ክፉ የሚያደርጉ ይስታሉ፥ ምሕረትና እውነት ግን መልካምን ለሚያደርጉ ናቸው።
ጠማማነት በልቡ አለ፥ ሁልጊዜም ክፋትን ያቅዳል፥ ጠብንም ይዘራል።
ክፉ አሳብን የሚያቅድ ልብ፥ ወደ ክፉ የሚሮጡ እግሮች፥
መበለቲቱንና ድኻ አደጉን፥ መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፤ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉ ነገር በልቡ አያስብ።
አንዱ በሌላው ላይ ክፉን ነገር በልቡ አያስብ፤ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፤ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል የጌታ ቃል።