ጌታ የወደደውን ይገሥጻልና፥ አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ።
አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ ሁሉ፣ እግዚአብሔርም የሚወድደውን ይገሥጻልና።
አባት የሚወደውን ልጁን እንደሚገሥጽ እግዚአብሔርም የሚወዳቸውን ሰዎች ይገሥጻል።
አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ እግዚአብሔር የሚወድደውን ይገሥጻል፥ የሚቀበላቸውን ልጆቹን ይገርፋልና።
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ጌታም ለሚፈሩት ይራራል፥
ለክፉ ሰው ጉድጓድ እስኪቈፈር ድረስ ከአስከፊ ዘመናት ይወገድ ዘንድ፥ አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ብፁዕ ነው።
በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፥ ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጸዋል።
ልጅህን ቅጣ ዕረፍትንም ይሰጥሃል፥ ለነፍስህም ደስታን ይሰጣታል።
እንግዲህ ሰው ልጁን እንደሚገሥፅ፥ እንዲሁም ጌታ እግዚአብሔር አንተን እንደሚገሥጽህ በልብህ አስተውል።
ጌታ የሚወደውን ይገሥጻልና፤ እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ሁሉ ይቀጣል።”
እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።