ምሳሌ 28:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለድሀ የሚሰጥ አያጣም፥ በድሆች ላይ ዐይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለድኾች የሚሰጥ አይቸገርም፤ አይቷቸው እንዳላየ የሚሆን ግን ብዙ ርግማን ይደርስበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለድኾች የሚሰጥ ከቶ አይቸገርም፤ ድኾችን ላለማየት ዐይኖቹን የጨፈነ ግን በሰዎች ዘንድ የተረገመ ይሆናል። |
እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤
“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ምድር ላይ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ ድኻ ቢኖር፥ በድኻ ወንድምህ ላይ ልብህን አትጨክንበት፤ ወይም እጅህን አትሰብስብበት።