ምሳሌ 28:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ደም ያለበት ሰው እስከጉድጓድ ይሸሻል፥ ማንም አያስጠጋውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው ደም ያለበት ሰው፣ ዕድሜ ልኩን ሲቅበዘበዝ ይኖራል፤ ማንም ሰው አይርዳው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው የሰውን ሕይወት ቢያጠፋ እስኪሞት ድረስ እየሸሸ ይኑር፤ ማንም ሰው አያስጠጋው። |
ኢዮአብ ወደ ጌታ ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ።
የሶርያም ንጉሥ ባርያዎች እንዲህ አሉት፦ “አምላካቸው የተራሮች አምላክ ነው፥ ስለዚህ በርትተውብን ነበር፥ ነገር ግን በሜዳ ላይ ከእነርሱ ጋር ብንዋጋ በእርግጥ እንበረታባቸዋለን።
‘ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ’ የሚል ነበር።” ስለዚህ ኢዩ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው” ሲል የቅርብ ረዳቱን አዘዘ።
አረማውያንም እባብ በእጁ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፥ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ከባሕርም ስንኳ በደኅና ቢወጣ የእግዚአብሔር ፍርድ በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም፤” አሉ።