ምሳሌ 27:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌላ ያመስግንህ እንጂ ከአንተ አፍ አይውጣ፥ ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌላው ያመስግንህ እንጂ የገዛ አፍህ አይደለም፤ ሌላ ሰው ያወድስህ እንጂ የገዛ ከንፈርህ አይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎች ሰዎች ያመስግኑህ እንጂ ራስህን አታመስግን፤ ሰዎች ስለ አንተ ይመስክሩ እንጂ፥ አንተ ስለ ራስህ መልካምነት አትናገር። |
ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን መቁጠር ወይም ራሳችንን ማስተያየት አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ እርስ በራሳቸው ሲያመዛዝኑ፥ እርስ በራሳቸውም ሲተያዩ፥ አስተዋይ አይደሉም።
በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።