ምሳሌ 27:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዳጅህንና የአባትህን ወዳጅ አትተው፥ በመከራህም ቀን ወደ ወንድምህ ቤት አትግባ፥ የቀረበ ወዳጅ ከራቀ ወንድም ይሻላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዳጆችህን ወይም የአባትህን ወዳጆች አትርሳ፤ ችግር ሲደርስብህ የወንድምህን ርዳታ አትጠይቅ፤ ከሩቅ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጐረቤት ይጠቅምሃል። |
በጌታዬ በንጉሡ ፊትም የእኔን የአገልጋይህን ስም አጥፍቶአል፤ ንጉሥ ጌታዬ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለሆንህ ደስ ያሰኘህን አድርግ።
ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በጌታ ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፥ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን ከሞት አተረፈ።
እንዲሁም ንጉሡ ኢዮአስ ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፥ ልጁንም ዘካርያስን አስገደለው፤ እርሱም ሲሞት፦ “ጌታ ይየው፥ ይበቀለውም” አለ።