ጉድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥ ድንጋይንም የሚያንከባልል ይገለበጥበታል።
ጕድጓድ የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ ድንጋይ የሚያንከባልልም ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል።
ለሌሎች ወጥመድን የሚዘረጉ ሰዎች ራሳቸው ይያዙበታል፤ በሰው ላይ የሚሰዱት የድንጋይ ናዳ እነርሱን መልሶ ይጐዳቸዋል።
በክፉዎች ትዕቢት ምስኪኖች ይሰደዳሉ፥ ባሰቡት ተንኰላቸው ተጠመዱ።
አምላክ ሆይ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፥ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።
ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ፥ በጽዮን ልጅ በደጆችዋ በማዳንህ ደስ ይለኛል።
ቅኖችን በክፉ መንገድ የሚያስት፥ እርሱ ወደ ጉድጓዱ ይወድቃል፥ ፍጹማን ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ።
ክፉ በክፋቱ ይጠመዳል፥ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።
ጉድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥ ቅጥርንም የሚያፈርስን እባብ ትነድፈዋለች።
በደለኞች ወዮላቸው፤ ጥፋት ይመጣባቸዋል፤
ኢየሩሳሌም ተንገዳገዳለች፤ ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው ጌታን የሚቃወም፤ የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና።