የጆሮ ጠቢ ቃል እንደ ጣፋጭ መብል ነው፥ እርሱም እስከ ሆድ ጉርጆች ድረስ ይወርዳል።
የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጕርሻ ነው፤ ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል።
የአሾክሻኪ ቃል እንደ ጣፋጭ ምግብ ደስ እያሰኘ እስከ ውስጥ ሰውነት ይወርዳል።
ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ሰውን አትገናኘው።
ሐሜተኞች ሰዎች ደምን ሊያፈስሱ በአንቺ ውስጥ ነበሩ፥ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፥ በመካከልሽ ሴሰኝነትን አደረጉ።
በሕዝብህ መካከል በሸንጋይነት ወድያና ወዲህ አትመላለስ፤ በባልንጀራህም ሕይወት ላይ መሰነናክል ሆነህ አትቁም፤ እኔ ጌታ ነኝ።