ሞኝን ወይንም አላፊ አግዳሚውን የሚቀጥር ሰው ነው፥ ሁሉን እንደሚያቆስል አዳኝ ነው።
ሞኝን ወይም የትኛውንም ዐላፊ አግዳሚ የሚቀጥር፣ ፍላጻውን በነሲብ እየወረወረ ወገኖቹን እንደሚያቈስል ቀስተኛ ነው።
በመንገድ የሚተላለፉትን ሞኞች ወይስ ሰካራሞች ሁሉ የሚቀጥር አሠሪ ያገኘውን ሰው ሁሉ እንደሚያቈስል ቀስት ወርዋሪ ነው።
እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ ፍዳውን የሚቀበል ከሆነ፥ ይልቁንስ ክፉዎችና ዓመፀኞችስ እንዴት ይሆኑ!
ወደ ሞኝነቱ የሚመለስ ሰው፥ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ ነው።
በሞኝ የሚነገር ምሳሌ፥ በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው።
እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል፤