ምሳሌ 25:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በንጉሥ ፊት አትመካ፥ በታላላቆችም ስፍራ አትቁም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በንጉሥ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ በታላላቆች መካከል መገኘትም አይመርህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንጉሥ ፊት በምትቆምበት ጊዜ ዝነኛ ለመሆን አትሞክር፤ ወደ ታላላቅ ሰዎችም ደረጃ ከፍ ለማለት አትፈልግ። |
ነገር ግን በተጠራህ ጊዜ፥ የጠራህ መጥቶ ‘ወዳጄ ሆይ! ወደ ላይ ውጣ’ እንዲልህ፥ ሄደህ በዝቅተኛው ስፍራ ተቀመጥ፤ ያን ጊዜም ከአንተ ጋር በተቀመጡት ሁሉ ፊት ክብር ይሆንልሃል።
ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ስለ ራስህ የነበረህ ግምት ታናሽ የነበር ቢሆንም፥ የእስራኤል ነገዶች መሪ አልሆንክምን? ጌታም በእስራኤል ላይ ቀብቶ አንግሦሃል።