Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 25:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በንጉሥ ፊት በምትቆምበት ጊዜ ዝነኛ ለመሆን አትሞክር፤ ወደ ታላላቅ ሰዎችም ደረጃ ከፍ ለማለት አትፈልግ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በንጉሥ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ በታላላቆች መካከል መገኘትም አይመርህ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በንጉሥ ፊት አትመካ፥ በታላላቆችም ስፍራ አትቁም፥

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 25:6
15 Referencias Cruzadas  

ሌሎች ሰዎች ያመስግኑህ እንጂ ራስህን አታመስግን፤ ሰዎች ስለ አንተ ይመስክሩ እንጂ፥ አንተ ስለ ራስህ መልካምነት አትናገር።


ብዙ ማር. መብላት መልካም አይደለም፤ እንዲሁም ከሰው ክብርን ለማግኘት መፈለግ አያስከብርም።


ከትዕቢተኞች ጋር የዘረፉትን አብሮ ከመካፈል ትሑት ሆኖ በድኽነት መኖር ይሻላል።


ሙሴ ግን እግዚአብሔርን “ወደ ፈርዖን ሄጄ የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ለማውጣት እኔ ማን ነኝ?” አለ።


እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዐይኖቼም ትዕቢተኞች አይደሉም፤ ስለ ታላላቅ ነገሮች ወይም ላስተውለው ስለማልችለው ከባድ ነገር አልጨነቅም።


ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንተ ስለ ራስህ የነበረህ ግምት አነስተኛ ቢሆንም የእስራኤል ነገዶች መሪ አልሆንክምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቀብቶ አንግሦሃል፤


“አንድ ሰው ለሠርግ ግብዣ ሲጠራህ በክብር ስፍራ አትቀመጥ፤ ምናልባት ከአንተ የበለጠ ክብር ያለው ሰው ተጠርቶ ይሆናል፤


ነገር ግን ለግብዣ ስትጠራ ሄደህ በዝቅተኛ ስፍራ ተቀመጥ፤ በዚያን ጊዜ የጠራህ ሰው ወደ አንተ መጥቶ፦ ‘ወዳጄ ሆይ! ወደ ከፍተኛው ስፍራ ወጥተህ ተቀመጥ’ ይልሃል፤ ያን ጊዜም በሌሎች ተጋባዦች ሁሉ ፊት ክብር ታገኛለህ።


ከንጉሥ ፊት ክፉ ሰዎችን አስወግድ፤ መንግሥቱም በፍትሕ ጸንታ ትኖራለች።


ከአንተ ለበለጠ ሰው ስፍራህን እንድትለቅ በሹም ፊት ተጠይቀህ ከምታፍር ይልቅ “ና ወደ ላይ ከፍ በል!” ብትባል ይሻልሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios